top of page

 

እግዚአብሔር አምላክ ማደሪያው ሁሉ ንጹሕና ቅዱስ ፍጹምም ነው።ስለሆነም እርሱ ያደረበ ሰውም ሆነ ቦታ ወይንም ንዋይ ሁሉ ቅዱስ ይባላል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምየአምላክ ማደሪያ ሆና ስለተገኘች ቅድስት ትባላለች ። የተገኘችውም እግዚአብሔ ካደረባቸው ቅዱሳን ስለሆነም ጭምር ቅድስት ተብላለች።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
• ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች
• ግንቦት 1 ቀን ተወለደች
• ታህሳስ 3 ቀን ወደ ቤተመቅደስ ገባች
• መጋቢት 29 ቀን አምላክን በድንግልና ፀነሰች
• ታህሳስ 29 ቀን አምላክን በድንግልና ወለደች
• የካቲት 16 ቀን የምሕረት ቃል ኪዳን ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከጌታችን
• ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ተቀበለች
• ጥር 21 ቀን በክብር አረፈች
• ነሐሴ 14 ቀን በክብር ተቀበረች
• ነሐሴ 16 ቀን እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነስታ ዐረገች መዝ.131፡8

                   የዐቢይ ፆም ሳምንታት 

      ዘ ወረደ

      ቅድስት

      ምኩራብ

መጻጉዕ

ደብረ ዘይት

ገብር ሄር

ኒቆዲሞስ

ሆሳህና

የቅዱሳን ታሪክ

 

 

 

ዳግም ምጽአት ‹‹ደገመ›› እና ‹‹መጽአ›› ከሚሉ ሁለት የግዕዝ ግሦች የተዋቀረ ሐረግ ነው፡፡ የጌታችንንና የአምላካችንን ለሁለተኛ ጊዜ ወደዚህች ዓለም መምጣት ያመለክታል፡፡ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ዳግምነቱ ለልደቱ ነው፡፡ ማለትም ልደቱን ‹‹ቀዳማዊ ምጽአት›› ካልን ዘንድ ለፍርድ መምጣቱን ‹‹ዳግም ምጽአት›› እንላለን፡፡

ጾም ማለት ሰውን ከምግብ መከልከል ነው፡፡ ፍት.አን.15 “ጾምሰ ተከልኦተ ብዕሊ ዕምመብልዕ በጊዜ እውቅ” ጾም ማለት በታወቀው ዕለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው፡፡ መብል መጠጥ...

1. ጸሎተ ነግህ

2.ጸሎተ ሠለስት

3.ቀትር(6 ሰዓት)

4.ተሰዓተ ሰዓት (9 ሰዓት)

5.ጸሎተ ሰርክ (11 ሰዓት)

6.ጸሎተ ንዋም (የመኝታ ጊዜ ጸሎት)

7.መንፈቀ ሌሊት (እኩለ ሌሊት)

የምንሠራውና የምናሻሽለው አይደለም  ከታኅሣሥ 29 ቀን ጀምሮ እስከ ዐቢይ ጾም መግቢያ ድረስ ያለው ወቅት /ጊዜ/ ዘመነ አስተርእዮ /የመገለጥ ወራት/ እየተባለ ይጠራል፡፡ በታኅሣሥ 29 ቀን የጌታችን ልደት ስለሆነ በዚህ አምላክ በሥጋ የተገለጠበት በዓል ይከበራል፡፡ ጥር 11 ቀን ደግሞ በጌታችን ጥምቀት የሥላሴ አንድነት ሦስትነት በይፋ የተገለጠበት ነው፡፡

© 2007 modefid by yeabtsega

  • w-facebook
  • Twitter Clean
  • w-vimeo
bottom of page