
የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ




የመላዕክት አለቃ

የመላዕክት አለቃ ገብርኤል ቅዱስ
የምስራች ነጋሪ መጋቢሐዲስ
በዙሪያቸው ከሞት የሚፈሩትን
ይታደጋቸዋል ከሥቃይ እቶን
እሳቱን አጥፍቶ በበትረመስቀሉ
ሲዘምሩ ዋሉ ይትባረክ እያሉ
መከራው ጸንቶብን ጨንቆን ስንጠራው
ሳይዘገይ ይደርሳል በግሩም ግርማው
ግና በሐጥያት ብናስመርረው
ይቀስፈናል የአምላክ ሲም በእርሱ ላይ ነው
·ዕለቱ አርብ ነው!
ኢየሱስ ይሰቀል!
ይሰቀል ኢየሱስ!
በርባን ግንይፈታ
!2 ሺህ ዘመን
ይኸው ትጮሃለች
ዓለም አፍ አውጥታ።
በቀያፋ ምክር
በካህናት አድማ
በጲላጦስ ስልጣን
በግፈኞች ጡጫ
ዛሬም ይወገራል
ጌታ ይሰቀላል።
እውነት ነው!
በድምጽ ብልጫና
በቲፎዞ መድረክ
ለምትመራ ዓለም
ሌባውን አንግሶ
ንፁሁን ከመሸጥ
ሌላ አይጠበቅም።
መጋቢት 2006 .ዓም
"ይሰቀል!"
Contact Us

በ Facebook ያግኙን
የተዋህዶ ልጆች
ጾም ማለት ሰውን ከምግብ መከልከል ነው፡፡ ፍት.አን.15 “ጾምሰ ተከልኦተ ብዕሊ ዕምመብልዕ በጊዜ እውቅ” ጾም ማለት በታወቀው ዕለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው፡፡ መብል መጠጥ...
ዳግም ምጽአት ‹‹ደገመ›› እና ‹‹መጽአ›› ከሚሉ ሁለት የግዕዝ ግሦች የተዋቀረ ሐረግ ነው፡፡ የጌታችንንና የአምላካችንን ለሁለተኛ ጊዜ ወደዚህች ዓለም መምጣት ያመለክታል፡፡ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ዳግምነቱ ለልደቱ ነው፡፡ ማለትም ልደቱን ‹‹ቀዳማዊ ምጽአት›› ካልን ዘንድ ለፍርድ መምጣቱን ‹‹ዳግም ምጽአት›› እንላለን፡፡
የምንሠራውና የምናሻሽለው አይደለም ከታኅሣሥ 29 ቀን ጀምሮ እስከ ዐቢይ ጾም መግቢያ ድረስ ያለው ወቅት /ጊዜ/ ዘመነ አስተርእዮ /የመገለጥ ወራት/ እየተባለ ይጠራል፡፡ በታኅሣሥ 29 ቀን የጌታችን ልደት ስለሆነ በዚህ አምላክ በሥጋ የተገለጠበት በዓል ይከበራል፡፡ ጥር 11 ቀን ደግሞ በጌታችን ጥምቀት የሥላሴ አንድነት ሦስትነት በይፋ የተገለጠበት ነው፡፡
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ
የቅዱሳን ታሪክ




ነገረ ቅዱሳን
1. ጸሎተ ነግህ
2.ጸሎተ ሠለስት
3.ቀትር(6 ሰዓት)
4.ተሰዓተ ሰዓት (9 ሰዓት)
5.ጸሎተ ሰርክ (11 ሰዓት)
6.ጸሎተ ንዋም (የመኝታ ጊዜ ጸሎት)
7.መንፈቀ ሌሊት (እኩለ ሌሊት)
መዝሙር አለቀሰየያሬድ ዝማሬ፣ የአዘማመር ስልቱ
የበገናው ቃና፣ማሲንቆ ቅኝቱ
የከበሮው ውበት የዋሽንት ፍሰቱ፡
ነበር ተፈጥሯቸው ስብሐት ሊዘሩ
ሥርዓት ሊያከብሩ
መንፈስን አድሰው ውበት ሊደምሩ
ምህላ ሊያደርሱ ኑዛዜ ሊያወሩ
ስንዱዋ እመቤት ቤተ ክርስቲያን ቅድስት
እንዳላስተማረች ሁሉን በሥርዓት
ዛሬማ አፍ የፈታ ሁሉ እያንጎራጎረ፣
ቀኖና ትውፊቱን እየሸረሸረ
የመዝሙር ሥርዓቱ ስልቱ ተቀየረ
መዝሙር ዜማ ሳይሆን ጩኸት ሆኖ ቀረ
ለነፍስ ሐሴት ትቶ ለሥጋ አደረ
ሳኦልም ከደዌው እንዳልተፈወሰ
ወኅኒውም በመዝሙር እንዳልፈራረሰ
መዝሙር ቅዱሳንን እንዳላወደሰ
ዜማን ሐዘን ገባው መዝሙር አለቀሰ
ንጉሥ ገብረ መስቀል ጦር ከእግር ሰክቶ
በፍጹም ተመስጦ አለምን ረስቶ
እንዳልነበር ሁሉ ጸጋችን ምግባችን
መዝሙር አንገት ደፋ ከመላእክት በላይ አዋቂዎች ሆነን
ሳይጠፋ መዝሙሩ እስከ ሥርዓቱ
ፈር እየለቀቀ ዘማሪ ነኝ አለ ሁሉም በየቤቱ
በጠፋበት ሁሉ ተሰጥኦው መክሊቱ
መዝሙር አለቀሰ ተገፍቶ መብቱ
ተጥሶ ሥርዓቱ።